በቻይና ፡ አንድ ተማሪ የንግግር ነፃነትን ለመከላከል ጫማውን ወረወረ

አንድ የሃይናን ዩንቨርስቲ ተማሪ በኦክቶበር 7፣ 2012 ዓ.ም በቻይና የመናገር ነፃነት አለመኖርን ተቃውሞ ሲማ ናን በተባሉ ማኦይስት ሀያሲ ላይ ጫማውን ወረወረ፡፡ ጫማውንም ከመወርወሩ በፊት ‹‹ምንም እንኳን የምትናገረው ጥሩ ነገር ባይሆንም፣ ወደ ሆቴልዎት መመለስ ይችላሉ፤ ነገር ግን እኔ ንግግሩን ብቃወም ትንሽ ጨለማ ክፍል ውስጥ እንደሚዘጋብኝ እርግጠኛ ነኝ ፡፡›› ብሏል፡፡

ተማሪው ርምጃውን የወሰደው በጥያቄ እና መልስ ሰዓት ነው፡፡ ከዚህ በታች ያለው ሁኔታውን የሚያሳየው አጭር የተማሪውን ንግግር የሚያስቀምጥ ፅሁፍ ነው፡
‹‹ከሁሉ አስቀድሜ አቶ ሲማ ናንን እንኳን ወደ ሀይናን ዩንቨርስቲ በሰላም መቱ ለማለት እፈልጋለሁ፡፡ እኔም እዚህ ተማሪ ነኝና፡፡ አንዳንድ ጉዳዩችን ማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡ በመጀመሪያ በአንድ ወቅት ስለ ሶቅራጠስ አንብቤለሁ በአንድ እናም እኔ ማውቀው አለማወቄን ነው ይላል፡፡ በሁለተኝነት እኔ ነፃነት እና ዲሞክራሲን እንደ ነፃነቴ ማስጠበቂያ እፈልጋቸዋለሁ፡፡ በሶስተኝነት እርስዎ ዲሞክራሲን ተቃርነው የተናገሩት ንግግር ነፃነቴን እንደተጋፋኝ ለመናገር እፈልጋለሁ፡፡ እኛ በእኩልነት ነፃነታችንን ማራመድ አልቻልንም፡፡  በፖለቲካ ትክክለኝነታቸው ምክንያት እርስዎ ካስቀመጡዋቸው አራት ነትቦች ተቃርኝ አልቀመጥም፡፡ ምንም እንኳን የምትናገረው ጥሩ ነገር ባይሆንም፣ ወደ ሆቴልህ መመለስ ትችላለህ፡፡ ነገር ግን እኔ ንግግሩን ብቃወም፣ ትንሽ ጨለማ ክፍል ውስጥ እንደሚዘጋብኝ እርግጠኛ ነኝ፡፡ እባክዎትን አያቋርጡኝ፡፡ ሰው ሲናገር አለማቋረጥን መልመድ ይኖርብዎታል፡፡ የኔ ጥያቄም እንደሚከተለው ነው፤ ጫማየን ወደ እርስዎ መወርወር እችላለሁ? በዚህ ሀገር ነፃነቴን ተገፍፌያለሁ፣ እናም እዚህ የመጣሁት ነፃነቴን ለማስጠበቅ ነው፡፡››

ሌላ ተማሪ በወቅቱ ነበረውን ሁኔታ በጦማሩ ሲገልፅ:

ስብሰባ የተጀመረው በ7፡30 ነበር፡፡ ሲጀመርም ሲማ ናን የዩንቨርስቲውን አስተዳዳሪ ሊ ጂንባዎንን በማወደስ ጀመሩት፡፡ በእውነት ማካበድ ይችሉበታል፡፡ የአስተዳዳሪው ስብእናም በቅፅበት ማደግ ጀመረ፡፡ አሰከትለውም በጣም ግልፅ ለመምሰል ሞከሩ እናም አንዳንድ ሰዎችም የተለያዩ ነገሮችን ሊወረውሩ እንደሚችሉ ይገባኛል አይነት ሀሳብ በማምጣት፤ ለዛም ዝግጁ እንደሆኑ ገለፁ፡፡

ከዛም አራት ነጥቦችን ብቻ አስቀምጠው ቀሪውን ጊዜ ለጥያቄ እና መልስ እንደሚያዉሉት ቃል ገቡ፡፡ ሞኝነቴን የተረዳሁት ዘግይቸ ነው፡፡ ንግግራቸው ረጅም፣ አሰልች እና በስህተቶች የተሞላ ነበር፡፡ አራት ነጥብ ያሉትም 1. በፓርቲ አመራር ውስጥ ብዙ ማህበራዊ ችግሮች ይኖራሉ 2. የፓርቲው አመራሮች ብዙ ስኬቶች እንዳስመዘገቡ 3. ያለ ፓርቲ ህብረተሰቡ ማጥ ውስጥ እንደሚዘፈቅ 4 የዜጎች ዲሞክራሲ ከፓርቲው አመራር መነጠል እንደማይችሉ ናቸው፡፡ […] በንግግራቸው መካከልም አንድ ሰው ወደ አዳራሹ ሊገባ ሲል በጠባቂዎች ተከለከለ፡፡

ጡዘቱ ያልተጠበቀ ነበር፡፡ ከአንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ንግግር በኋላ ሲማ ናና ንግግራቸውን አቆሙ፡፡ የጥያቄ እና መለስ ጊዜውም ተጀመረ፡፡ ከኔ ፊት ለፊትም አንድ ብርቱካናማ የስፖርት ልብስ ለበሰ ሰው መናገር ጀመረ፡፡ ንግግሩንም ከግሪኩ ፈላስፋ ሶቅራጠስ ንግግር ጠቅሶ ጀመረ፡፡ ዝርዝር ሁኔታዎችን አስገራሚ ስለነበሩ ዘንግቻቸዋለሁ፡፡ የንግግሩ ዋነኛ ነጥብም ነፃነት እና እኩልነት ነበር፡፡ ሰውየው ሲናገር በመናገር ነፃነት በኩል እኩል መብት የለንም፣ ነፃነት የለኝም፣ እርስዎ የተናገሩት ነገር በፖለቲካዊው ምልከታ በኩል ትክክል ነው፡፡ ምንም እንኳን የተናገሩት ጥሩ ነገር ባይሆንም፣ ወደ ሆቴልዎት መመለስ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን እኔ ንግግሩን ብቃወም ትንሽ ጨለማ ክፍል ውስጥ እንደሚዘጋብኝ እርግጠኛ ነኝ ፡፡ (ይህ እኔ ላስታውስ የቻልኩት ነገር ነው፣ አዝናለሁ) ፡፡ ሲማ ናን አስከትለው ይህ ጥያቄ አይደለም አሉ፡፡ ተማሪውም ሲመልስ የኔ ጥያቄ ይሄው ነው፣ ጫማየን መወርወር እችላለሁ; ከዛም በቁርጠኝነት የለበሰውን የስፖርት ጫማ ወደ መድረኩ ወረወረ፡፡ እኔም ሳላስበው አጨበጭብ ነበር…

 

ሲማ ናን ማኦይስት ሲሆኑ ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ የሰሜን ኮሪያ ሞዴል በጫይናም እንዲዳብር እና በውጭ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አካሄድ እንዲኖር ይፈልጋሉ፡፡ በተጨማሪም ለዘብተኞች ላይ የጥላቻ ንግግር በማድረግ እና የሀገሪቱ ስጋቶች ናቸው በሚል ውንጀላቸው ታዋቂ ናቸው፡፡

ብዙ ተማሪዎች የተማሪውን ደፋር ተግባር ያደነቁ ሲሆን አንዳንዶች ግን የተማሪው ደህንነት አሳስቧቸዋል፡፡ ከዚህ በታች በድረ ገፅ ስለሁኔታው የነበረውን ውይይት በኔ ምርጫ አቅርቤያለሁ:

慕容雪村 : ሲማ ናን እራሳቸውን ማኦይስት ርዕዮተ ዓለም እንደሚከተል ምሁር ይቆጥራሉ፡፡ ምንአልባትም በማኦ ዘመን ስለተካሄደው ማሰቃየት እና ጥቃት ዘንግተውት ይሆናል፡፡ – በዛን ወቅት ሰዎች ረጅም ኮፍያ አጥልቀው በመንገድ ይነዱ ነበር፣ በብረት ቀበቶም ይገረፉ ነበር ፣ከብት በመጠበቅ ስራ ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ ስህተታቸውን እንዲያምኑ ይደረጉ ነበር፡፡ ዛነግ ዚን አንገቱን ተቆርጧል፣ ዋንግ ሰዊ በድብቅ ከተገደለ በኋላ ጉድጓድ ውስጥ ተቀብሯል፡፡ ላኦ  ሺ እና ፉ ሊ ራሳቸውን አጥፍተዋል… ጫማ ወደ እራሳቸው መወርወሩ ለእራሳቸው እንደ ሽልማት ነው፡፡

 

古月照兰芳፡ አንተ የሲማ ናንን ንግግር ስላልወደድከው ጫማ ወርውረሃል፤ እኔ የዊፎንጎንን ንግግር ስላልወደድኩት  እንቁላል እወረውራለሁ፤ አንተ ኦይንግ ዶንግን ስላልወደድክ ጭቃ ትወርውረሃል፤ እኔ ዛኦ ኦላይን ስላልወደድኩት፣ ድንጋይ እወረውርበታለሁ፤ አንተ የዞንግ ሀንግሊንግን ንግግር ስላልወደድክ፣ አስለቃሽ ጭስ ትወረውርበታለህ፤ እኔ ላኦ ንግን ንግግር ስላልወደድኩ፣ ቦምብ እወረውርበታለሁ፤ አንተ የሀን ዳንግሊንግንን ንግግር ስላልወደድክ፣ ኑክሌር ትለቅበታልህ – እንዲህ ነገሮችን እየተወራወርን ዲሞክራሲን እንገነባለን?

 

吴钩1975፡ በዊቦ ብዙዎች ስለ ተማሪው ድርጊት እየተከራከሩ ይገኛሉ፡፡ አንዳንዶች አጨብጭበዋል፣ ሌሎች ደግሞ የሌሎቹን መብት መጣስ ተገቢ አይደለም እያሉ ይተቻሉ፡፡ ጫማ ስለመወርወር ጉዳይ ስምምነት ላይ መድረስ ይኖርብናል፡፡ እኔ ጫማን መወርወር ጥቃት ነው ብየ አላስብም፤ ይልቅስ ደካማው ወገን ተቃውሞውን የሚገልጽበት መንገድ ነው፡፡ በምዕራብ ሀገሮች ወደ ባለስልጣናት እንቁላል መወርወር በጣም የተለመደ እና እንደ ጥፋት የማይይጠር ድርጊት ነው፡፡

 

十年砍柴: ሰዎች በተማሪው ድርጊት ደስ ሊላቸው አይገባም፡፡ በምእራብ ሀገሮች እንቁላል መወርወር መብት አካል ሲሆን ቅጣቱም እዚህ ግባ የማይባል ነው፡፡ ነገር ግን በቻይና አደጋው ብዙ ነው፡፡ ሲማ ናን ተማሪውን መቅጣት ስልጣን የለውም፡፡ ነገር ግን ድርጊቱን እንደ ተሞክሮ በመውሰድ ሌሎች ተማሪዎች ይሄን ድርጊት ስልጣኑ ያላቸው ሰዎች ላይ ከፈፀሙት፤ የሚከፍሉት ዋጋ ከባድ ነው፡፡

ንግግሩን ይጀምሩት

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.