ባህሬን፤ ዴሞክራሲና እስልምና አንድ ላይ መኖር ይችላሉ?

‘በኢስላማዊ ማኀበረሰብ ዴሞክራሲ ሊኖር ይችላል? ’ዛሬ  ይህ ርዕስ በባህሬናውያን ጦማሪዎች መካከል መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

ጉዳየን ያነሳው የባህሬናውው አርቲስት አል ሻክህ ትዊት በማድረግ ነው [ar]:

في المجتمعات الاسلامية من الصعوبةالفصل بين ماهو سياسي وديني ولذا لن تنجح الديمقراطيةحتى لو كتبنا افضل الدساتير وقبلنا بالتناوب السلمي للسلطة

@Anas_Al_Shaikh፤ በኢስላማዊ ማኀበረሰብ ውስጥ ፓለቲካ ምን አንደሆነ እና ሀይማኖት ምን እንደሆነ ለመለየት አስቸጋሪ ነው፤ ለዚህም ይመስላል ምንም እንኳን ምርጥ ህገ መንግስት ብናዘጋጅም ሰላማዊ የስልጣን ሽክርክርን ብንቀበል ዴሞክራሲ ተሳክቶልን የማያውቀው፡፡

ፊርለስ ባሪኒያ መለሰ፤

الديمقراطيةهي الحل و العلاج لمثل هذه المشاكل إذا تطورت القوانين سيتطور الناس بشكل طبيعي الدولة المدنية هي الخلاص لهذا الشعب

@fearlessbahrain፤  ለእንደዚህ አይነት ችግሮች ዴሞክራሲ መፍትሔና ፈዋሽ ነው፤ ህጎች ከተዘጋጁ በተፈጥሮዓዊ መንገድ እየተሻሻሉ ይመጣሉ፡፡የሲቪል ማኀበረሰብ የኛ ህዝብ መድህን ነው፡፡

ባህሬናዊው ጋዜጠኛ አባስ ቡሳፍዋን ሌላ መወሰድ አለው፤ ለአል ሻይክህ የመጀመሪያ ትዊት እንዲህ ሲል መለሰ፤

والله هالاستنتاج مؤلم، لكنه قد يكون تعميميا، ربما نجحت تجربة تركيا

@abbasbusafwan፤ ይህ ድምዳሜ በእውነት ያማል፤ ይህ በጅምላ መፈረጅ (generalization) ነው ፡፡ ምን አልባት ቱርክ የስኬት ተምሳሌት ልትሆን ትችላለች፡፡

አል ሻይከህ መለሰለት፤

تركيا لم توازن بين الشأن السياسي والديني والدليل ان هناك حقوق للشواذ وانا شفتهم بنفسي يتظاهرون في شارع “تقسيم” الشهير هههه

@Anas_Al_Shaikh፤ በቱርክ የሀይማኖት እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ሚዛናዊ አይደሉም፡፡ለምሳሌ በቱርክ የግብረ ሰዶማውያንን መብት  አለ፤ እናም እኔ ራሴ በታዋቂው ታክሲም ጎዳና ተቃውሞ አይቻለው፡፡

አህመድ አል ሓዳድም ጨመረበት

تـركيا ليست في عهد اليوم بل في زمان أتاترك // وتركيا اليوم وأردوغان الشهير أعادوها لما قبل أتتارك

@DiabloHaddad፤ ዛሬ ቱርክ በመራሔ አታቱርክ  እንደነበረችው አይደለችም፤ ታዋቂው ኤርዶጋን ቱርክን ወደ ቅድመ አታቱክ ዘመን መልሷታል፡፡

ቡሳፍዋን በመልሱ ቀለደ፤

اعتقد ان السعودية احسن نموذج للديمقراطية والشورى وحقوق الانسان والاعلام المقتوح والتوازن بين السياسي والديني!

@abbasbusafwan፤ ሳውዲ አረቢያ የዴሞክራሲ ምርጥ ምሳሌ ትመስለኛለች፤ ሹራ፣ ሰብዓዊ መብት፣ ነጻ ፕሬስ፣ በሀይማኖት እና ፓለቲካ መካከል ሚዛናውነት

አቡ ዮሲፍ በሃይማኖት እና ፖለቲካ አለመቀላቀል ይስማማል፤

انا معك،يجب ان لا نخلط الدين والسياسة فهم لا يتفقان،فنصبح نظام قمعراطي مثل ايران،

@xronos2፤ እስማማለው ሃይማኖት እና ፖለቲካን መቀላቀል የለብንም እነርሱ ግን አይስማሙም ከዚያም ልክ እንደኢራን ጨቋኝ ስርዓት ይኖረናል፡፡

አቡ ካሪም የምዕራባውያን የዴሞክራሲ ዘዬ  ከውጭ ከምናመጣ ያለንን ማሻሻል ይገባናል ይላል፤

مشكلتنا اننا نريد تطبيق النظريات الغربية على مجتمعاتنا بدل البحث عن ما يوجد لدينا وتحديثه

@AbuKarim1፤ ችግራችን ያለንን ከማሠስ እና እርሱን ከማዘመን ይልቅ በእኛ ማኀበረሰብ ላይ የምዕራባውያንን ንድፈ ዐሳብ  ለመተግበር እንፈልጋለን፡፡

3 አስተያየቶች

ምላሹን ያጥፉ

ንግግሩን ይቀላቀሉ -> Mubharik

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.