ቻይና በአፍሪካ፤ እውነተኛው ታሪክ

ሒቢስከስ የቻይና እና አፍሪካ ግንኙነትን በተመለከተ ነገረ ውይይቶችን በመስመር ላይ ለማስተጋባት የተፈጠረ ‘የዓለም ድምጾች’ (Global Voices) ፕሮጀክት ነው፡፡ በተለይም ደግሞ በሁለቱም ክልሎች ያሉ ጦማሪዎች እና ከዚያም ውጪ ያሉትን የጋራ ውይይትን ለማበረታታት ይሠራል፡፡

የቻይና ትኩረት በአፍሪካ ላይ በከፍተኛ ፍጥነት የጨመረው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሲሆን አሁን አገሪቱን የአፍሪካ ትልቋ የንግድ ሸሪክ አድርጓታል፡፡ “በቻይና እና አፍሪካ መካከል የተደረገው የንግድ ልውውጥ ባለፉት 5 የ2012 ወሮች ውስጥ የዓመት ለዓመት ንፅፅሩ በ22 በመቶ ሲያድግ መጠኑ 80.5 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ” በማለት የቻይና የንግድ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ማይክ ኪንግ ጽፏል፡፡

የዚህ ፕሮጀክት አካል እንደመሆኑ፣ በቻይና-አፍሪካ ግንኙነት ላይ ያተኮሩ ጦማሮችን እና የማሕበራዊ መገናኛ ብዙሐን ትኩረቶችን በመደበኛነት እንዘግባለን፡፡ ዛሬም፣ ቻይና በአፍሪካ፤ እውነተኛው ታሪክ የሚለውን በዲቦራ ብሮቲጋም (የThe Dragon's Gift: The Real Story of China in Africa ድራሲ) የተጻፈውን ጦማር እናስነብባችኋለን፡፡

 

Banner in Beijing in November 1996, during the Forum on China-Africa Cooperation. Image released under Creative Commons (CC BY-SA 2.0) by Flickr user stephenrwalli

እ.ኤ.አ. በ1996 በቤጂንግ በተካሄደው የቻይና-አፍሪካ የትብብር መድረክ ላይ የተለጠፈ ባነር፡፡ ምስሉ የተለቀቀው በCreative Commons (CC BY-SA 2.0) stephenrwalli በተሰኘ የFlickr ተጠቃሚ ስም ነው

ዲቦራ ብሮቲጋም:

Professor and Director, ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ፣ የዓለም አቀፍ የልማት ፕሮግራም ፕሮፌሰር እና ዳይሬክተር ናቸው፤ በተጨማሪም የ IFPRI መራኄ ተመራማሪ ፌሎው፣ እና የ The Dragon's Gift: The Real Story of China in Africa (Oxford U. Press, 2009, 2011) ደራሲም ናቸው፡፡ የቻይና ምሁር ሲሆኑ፣ መጀመሪያ ወደ አፍሪካ የመጡት እ.ኤ.አ. በ1983 ለምርምር ሲሆን፣ ምርምራቸውን እስካሁን ገፍተውበታል፡፡

ቻይና በአፍሪካ፤ እውነተኛው ታሪክ የዳንዌይ አርአያ ሠራተኛ ሽልማት 2012 አሸናፊ ነው፤ ዳንዌይ ስለቻይና የተመረጡ ልዩ የድረአምባ፣ ጦማር እና የመስመር ላይ የመረጃ ምንጮች ዝርዝር ነው፡፡

ከዚህ በታች የምናቀርብላችሁ በዲቦራ ብሮቲጋም ስለቻይና በአፍሪካ መገኘት የተጻፉ ጥቂት ማራኪ ታሪኮች ነው፡፡

ቻይኒኛን በዛምቢያ መማር‘:

ቻይና በአፍሪካን በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ የመስክ ጥናት የሚያደርጉ ተማሪዎች ቁጥር እያደገ ነው፡፡ በቅርቡ ያነበብኩት አንድ የአርወን ሁግንቦሽ ኤም.ኤ. (በሊደን ተቋም) ጥናት ርዕሱ “Made-in-China: Chinese as a commodity and a socioeconomic resource in Chinese language schools in Zambia” የሚል ሲሆን፣ ሊያነቡት የሚገባ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡

አርወን ብዙ ወራት ያጠፋው በዛምቢያ የቻይና ቋንቋ ትምህርት ቤት “የተማሪዎችን/ተሳታፊዎችን አስተያየት” ሲያጠና ነው፡፡  (ትምህርት ቤቱ የኮንፉሺየሽ ተቋም እና ለትርፍ ያልተቋቋመ የቻይንኛ ቋንቋ ትምህርት ቤት አለው፡፡) አርወን አብረውት ለተለያየ ዓላማ እና ተስፋ ውስጥ ቻይኒኛ ያጠኑ ተማሪዎችን ሪፖርት አይቷል፡፡

ተመራማሪዋ ቀጥለውም ይናገራሉ:

የአርወን ትንታኔ እንደሚያስረዳው፣ ዛምቢያዎች ቻይኒኛ የሚያጠኑት አርቀው በማሰብ ነው፡፡ አንዳንዶች የሥራ አድማሳቸውን እንደሚያሰፋላቸው ያስባሉ፤ ነገር ግን አርወን በጽሑፉ እንዲህ ይላል፡ “የቻይና ኩባንያዎች በቻይና የሰለጠኑ ተቀጣሪዎችን ይፈልጋሉ፡፡” አርወን ከሚችለው ቻይኒኛ የተሸለ የሚናገሩ ብዙ አፍሪካውያን ሳይኖሩ አይቀሩም፡፡ አሁን ኢትዮጵያ ነው ያለሁት፤ በኢትዮጵያ ያሉ የቻይና ኩባንያዎች ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን በከፍተኛ የአስተዳደር ኃላፊነት ሳይቀር ሲቀጥሩ ማየቴ አስገራሚ ምሳሌ ነው፡፡ የአንድ አምራች ድርጅት የምርት ኃላፊ ኢትዮጵያዊ ነው፤ ቻይናዊው/ዋ የፋብሪካው ባለቤት በሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ማሊ እና ሌሎች በርካታ የአፍሪካ አገራት ፋብሪካዎች ስላሉዋቸው፣ ኢትዮጵያዊው ኃላፊ የኢትዮጵያውን ፋብሪካ በራሱ ያስተዳድራል፡፡

የኬንያ ነጋዴዎች አመጽ በተፎካካሪዎቻቸው ላይ‘:

የቻይና ነጋዴዎች በአፍሪካ ገበያ ውስጥ ዘልቆ መግባት በአፍሪካ-ቻይና ግንኙነት ላይ አላስፈላጊ አሻራ ያሳርፋል፡፡ ይህ ቪዲዮ የሚያሳየው የአፍሪካ ነጋዴዎች የቻይናን ፉክክር ፍራቻ፣ በቅርቡ በናይሮቢ ያደረጉትን ተቃውሞ ነው፡፡ ሸማቾች በጥቅሉ በርካሽ ዋጋ ሸቀጦች መቅረቡን በፀጋ ይቀበሉታል፤ ነገር ግን የርቃሽ ሸቀጦችን አነስተኛ ጥራት በየቂዜው ማማረራቸውም አልቀረም፡፡

በበጎ ጎኑ ስንመለከተው ደግሞ፤  በፓይራሚዱ መቀመጫ ላይ ያሉ አፍሪካውያንን ርካሾቹ የቻይና ተንቀሳቃሽ ስልኮች ባልተጠበቀ ቁጥር ተጠቃሚ አድርገዋቸዋል፡፡ በተቃራኒው፣ የመድሃኒት አምራቾች — የተለመደ ክስተት ነው — በሽታን ሲያባብሱ ወይም ከሞት ሳያድኑ ይቀራሉ፡፡ ይህ ሁሉንም የቻይና መድሃኒቶችን እምነት በማሳጣት የመድሃኒቶች የውጭ ገበያቸው ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ያሳርፋል፡፡ በእርግጥ እነዚህ ሁሉ ሸቀጦች በቻይኖቹ ሻጭነት ገበያ መውጣት አይጠበቅባቸውም፤ ቀደም ሲል እንደጠቀስኩት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የአፍሪካ ነጋዴዎች የቻይና ከተሞችን እየጎበኙ እና ከቻይና ወደአገራቸው ሸቀጦችን በመላክ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል፡፡

ኤንቲቪኬንያ ላይ በኦገስት 16፣ 2012 ዩቱዩብ ላይ የተለጠፈው ቪዲዮ አፍሪካውያን ነጋዴዎች የቻይና ተፎካካሪዎቻቸውን ሲቃወሙ ያሳያል:

“ዞምቢ” የቻይኖች መሬት መቀራመት በአፍሪካ እንደገና በአዲስ የመረጃ ቋት እያደገ ነው!‘:

ባለፈው ሳምንት፣ አዲሱ የመሬት ማትሪክስ “የመሬት መቀራመት” የመረጃ ቋት በትልቁ የዓለም ባንክ የመሬት አውደጉባኤ ላይ ታይቶ ነበር፡፡ የመሬት ማትሪክሱ ፕሮጀክት “የአውሮፓ ምርምር ማዕከልን እና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ 40 የሲቪል ማሕበራትና ተመራማሪዎች ቡድንን ዓለም አቀፍ ትብብር” ነው፡፡ በጥናቱ፣ ጠንካራ አዘገጃጀት እና መካተት ስላለባቸው ፕሮጀክቶች በጣም ቀጥተኛ መመዘኛ አላቸው፡፡ በተግባር ግን፣ የገዛ መመዘኛቸውን በተደጋጋሚ ሲጥሱት ታይተዋል፤  ቢያንስ በአፍሪካ ያሉ የቻይና “ፕሮጀክቶችን” በተመለከተ፡፡

የቻይኖቹ “ዞምቢዎች” መሬት ወረራ በአፍሪካን ተመራማሪዋ በጥልቀት ሲዘረዝሩት:

በእስያ፣ በተለይም በካምቦዲያ እና በሌኦስ ብዙ የቻይኖች መሬት ኢንቨስትመንት እንዳለ ይገባኛል፡፡ የእስያውን ጉዳይ አላውቅም፤ የመረጃ ቋቱ ይፋ ሲወጣ ግን፣ የቻይና-አፍሪካን ጉዳይ ተመልከቼዋለሁ፡፡ እንደምትገምቱት “ሁለገብ” ዝርዝሮችን ብቻ ለጥሬ ሐቅ ማመሳከሪያነት ያስቀምጣል (ይህም ምናልባት ሌላ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት አጠራጣሪ መረጃ አውጥቶ ከሆነ ለማመሳከር ብቻ ይበጃል)፡፡ እኔ በጣም ፈልጌ የነበረው “ዞምቢዎቹን የቻይና ፕሮጀክቶች” ጉዳይ በመረጃ ቋታቸው ውስጥ እርግጡን ለማየት ነበር፡፡ (ያለቁ ፕሮጀክቶች፣ ወይም ለእነርሱ መኖራቸው እንኳን የማይታወቁትን ፕሮጀክቶችን ጉዳይ ማለቴ ነው) ይህን ምሳሌ ተመልከቱ:

(1) ZTE በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦቭ ኮንጎ፣ 2.8 ሚሊዮን ሄክታር  የፓልም ዘይት ፕሮጀክት አለው፡፡ ፕሮጀክቱ ተወርቶ ያውቃል ነገር ግን አልተጠናቀቀም፣ መሬት አልተሰጠውም፣ 100,000 ሄክታር ይፈጃል ቢባልም ጫፉም አልደረሰ፤ እናም ለዓመታት ሰጥሞ ቀርቷል፡፡

(2) ABSA Biofuels በኢትዮጵያ 30,200 ሄክታር አለው. ቀልድ? ይህ የጥምረት ፕሮጀክት የቻይኖች አይደለም፣ ነገር ግን የደቡብ አፍሪካዊ – ቻይናዊ  – ኢትዮጵያዊ ፕሮጀክት ነው፡፡ በ2008ቱ የመረጃ ቋት ውስጥም “በቅድመ-ተከላ” ደረጃ ያለ ተብሎ ተመዝግቧል፡፡ እስካሁን አልተጀመረም፡፡

(5) በዝምባብዌ 101,170 ሄክታር የበቆሎ ፕሮጀክት አለ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ተቆጥሮ የማያልቅ ጊዜ ጽፌያለሁ፡፡ በዝምባብዌ መንግስት ለቻይና የኮንስትራክሽን ኩባንያ የተሰጠ ውል ነው፣ የቻይና ኢንቨስትመንት አይደለም፡፡ አልተከፈላቸውም፡፡ ወደአገራቸው ገብተዋል፡፡ መሬቱ ለምቶ አልበቃውም፡፡ የፔቲ ያለህ፣ ይሄ የሆነው ከአሥር ዓመት በፊት ነው፤  እ.ኤ.አ. በ2003.

የአፍሪካ ነፃ ፕሬስ ችግር፤ ቻይና አመጣሽ ይሆን?‘:

በኤፕሪል 15፣ 2012 ኒው ዮርክ ታይምስ በተባባሪ አርታኤው ሞሐመድ ኬታ የአፍሪካ የነፃው ፕሬስ ችግር እየተባባሰ መሆኑን – ምክንያቷም ቻይና መሆኗን ጻፈ፡፡

የኬታ ጽሑፍ ብዙ ጥሩ ነጥቦችን ያነሳል፡፡ ምርምር አዘል ሪፖርት በአፍሪካ እጅግ ፈታኝ የሆነ መንገድ ከፊቱ ይደቀንበታል፤ እናም በማይቻለው ጎዳና ላይ ብዙ ደፋር እርምጃዎችን መውሰዱን መጥቀስ ይቻላል፡፡

በአስተያየቱ፣ ቻይና በአፍሪካ የምታደርገው ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴን እና የመገናኛ ብዙሐን መታፈንን ግንኙነት ለመዘርዘር ማስረጃዎችን አቅርቧል፡፡

“ለምን ይህ አስጨናቂ መገናኛ ብዙሐንን የማፈን እርምጃ አስፈለገ?” ሲል ይጠይቃል፡፡ ኬታ የሚመልሰው “ምዕራባውያንን በ2009 የበለጠው የቻይና-አፍሪካ የንግድ ሸሪክነት”ን እንደሰበብ በማስቀመጥ ነው፡፡

ለነዚህ ጉዳዮች ግንኙነት ምሳሌ ኬታ የሚያቀርበው፣ “በ2005 እና በ2009 መካከል የቻይና እና ሩዋንዳ የንግድ ግንኙነት በ5 እጥፍ አድጓል፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ፣ የሩዋንዳ መንግስት ሐያሲ ፕሬሶችን ማፈንና ከፍተኛ የተቃዋሚ ድረአምባዎችን የማገድ ሥራ ሰርቷል፡፡”

ተመራማሪዋ፣ የአፍሪካ መንግስት መገናኛ ብዙሐን አፈና እና የቻይኖች ቴክኒካዊ ድጋፍ ትስስርን በተመለከተ ከኬታ ጋር ይስማማሉ:

ኬታ ጥሩ ነጥብ ያነሳው እያደገ ባለ የንግድ ግንኙነት “ቻይና ሐያሲ ፕሬሶችን ለማፈን እና ቴክኒካል ድጋፍ በመስጠት ሁለቱም ኒዮ ኮሎኒያሊስት እያሉ በሚጠሩት ሰበብ ተሳስረዋል፡፡

የአፍሪካ ሪፖረተሮች እንደ ዢኖዋ ሪፖርተሮች እንዲሆኑ በማሰልጠን ፈንታ፣ የቻይናውያን ዓላማ በምዕራባውያን” ስለቻይና በአፍሪካ ኢንቨስትመንት የሚወራውን አሉታዊ ዜና የሚያስተባብል ስልጠና እና ማሕበራዊ ግንኙነት ላይ ማተኮር ይዘዋል፡፡

የዘመናዊው ቻይና-አፍሪካ ግንኙነት የተመሰረተው እ.ኤ.አ. በ1950ዎቹ፣ ቻይና ከአልጄሪያ፣ ግብጽ፣ ጊኒ፣ ሶማሊያ፣ ሞሮኮ እና ሱዳን ጋር የጋራ ስምምነት ስትፈርም ነው፡፡ በርግጥ፣  ጥንታዊው የቻይና-አፍሪካ ግንኙነት ከክ.ል.በ. 202 እስከ 220 ድረስ ወደኋላ የዘለቀ ነው፡፡ በአርኪዮሎጂስቶች ቁፋሮ በሞቃዲሾ፣ ሶማሊያ እና ኪላዊ፣ ታንዛኒያ ጥንታዊ የቻይና ሳንቲሞች ተገኝተዋል፡፡

1 አስተያየት

ንግግሩን ይቀላቀሉ

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.