- Global Voices በአማርኛ - https://am.globalvoices.org -

ኢራን ጎግል እና ጂሜል እንዳይታዩ አገደች

Categories: መካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ, ኢራን, ቴክኖሎጂ, አመጽ, አስተዳደር, የንግግር ነፃነት, የዜጎች መገናኛ ብዙሐን, ፖለቲካ

የኢራናውያን ስርዓት ላለፉት አስርት ዓመታት ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ጠላት የነበረ ቢሆንም፣ አሁን እሁድ መስከረም 23 2012 እ.ኤ.አ.  ደግሞ  በሚቀጥሉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ጎግል እና ጂሜልን ማጥለል እንደሚጀምሩ በመግለጽ የበለጠ አስደምመውናል፡፡

 ኢራናዊው ባለስልጣን አብዶልሰመድ ኮራማባዲ እንደተናሩት እገዳው የተላለፈበተት ምክንያት [1] ህዝቡ ብዙዎች እንደ ስድብ ቃል የሚያዩት በዩቱዩብ የሚገኘውን ጸረ እስላም ፊልም [2] እንዲቃወሙ ነው (ዩቲዩብ የጎግል ንብረት ነው)፡፡ ኮራማባዲ  “የወንጀል ይዘት ያላቸው [3] ቅጽበቶች ድንጋጌ ኮሚሽን” ቁልፍ አባል ናቸው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ እንዳንዶች የጎግል መታገድ እውነተኛው ምክንያት ከመስከረም 22 ጀምሮ ስራ ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀውን [4] እስካሁን ግን ብቅ ያላለውን የኢራናውያን ብሔራዊ በየነ መረብ [5] የበለጠ ለማስተዋወቅ ነው ሲሉ ከወዲሁ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

Cartoon by Mana Neyestani. Source: <a href="http://www.facebook.com/InternetFreedomProject?notif_t=page_name_change">Internet Freedom Project on Facebook</a>

ካርቶን በማና ናይስታኔ  ምንጭ፡ የበየነ መረብ ነጻነት ፕሮጀክት በፌስቡክ [6]

የአለም ድምጸች  ቴህራን፣ ሺራዝ  እንዲሁም ቆምን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ በርካታ ኢራናውያንን አነጋግሯል፡፡ሁሉም ማለት ይቻላል ጂሜልን መጠቀም እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡በርካታ ቁጥር ያላቸው ደግሞ “ጎግል ፈልግ”ን መጠቀም እንዳልቻሉ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

መቀመጫውን በካናዳ ያደረገው ኢራናዊ ጦማሪ እና የኮምፒዩተር ተመራማሪ አራሽ አባደፑር [7] ለአለም ድምጾች ሁኔታውን እንደሚከተለው አብራርቷል፤

ጎግልን ማቋረጥ በእርግጠኝነት ብዙዎችን አማራጭ መንገድ እንዲፈልጉ ያደርጋቸዋል፡፡ የሂደቱም ውጤት የግድ በየነ መረብ “የተሻለ” ፣ “የበለጠ ነጻ” እንዲሆን ላይሆን ይችላል፡፡ግና ግና አሁን እየተካሄደ ያለው ተግባር  ኢራናውያን በሁለት እግራቸው እንዲቆሙ የሚረዳቸው አይደለም፡፡እነርሱ ህዝቡን እየገፉት ያሉት የበለጠ ጥንቃቄ ወደሚያሻው የበየነ መረብ አገልግሎት ነው፡፡ ለህዝቡ እየነገሩት ያሉት ይሄንን ነው “ሂዱ ቪፒኤን እንዴት መጠቀም እንዳለባችኹ ተማሩ”  እናም በእርግጠኝነት ምን እንደሚፈጠር መተንበይ እችላለው፡፡

የበየነ መረብ ነጻነትን እና ጎግል የመጠቀም መብትን ለመጠየቅ የፌስቡክ ዘመቻ ይፋ ተደርጓል [6]፡፡ጎግል ሲጠል የሚያሳየው የማና ነይስታኒ ካርቱንም (በቀኝ በኩል) በዚህ የፌስቡክ ገጽ አይነ ገብ ነው፡፡

በርካታ ኢራናውያን የበየነ መረብ ተጠቃሚዎች በውስጠ ዘ ስለማጥለሉ ተውተዋል፡፡ ባህራን ታጅዲን ይህን ትዊት [8] አደረገ [fa]፤

@Behrang፤ እነዚህ ጎግል እንዲጠል የጠየቁ “ህዝቦች” የጄሜል አድራሻ የላቸውም? ካላቸው ለምን ነበር የሚጠቅሟቸው ?

ሳዬ ሮሻን ትዊት [9] አደረገ[fa]፤

@sayeeeeh ፤ እኛ ጎግል እና ጂሜልን አግደናል፤ የዶላርን የዋጋ ተመን ከፍ አድርገናል፤ በዚህ ተግባራችን የአሜሪካዉያንን ህይወት ማክበድ እንደምንችል እጠራጠራለው፡፡

በእውነቱ የዚህ ውሳኔ ቀዳሚ ተጠቂ ጎግል ሳይሆን የኢራናውያን ነጻነት ነው፡፡ለእስላማዊ ስርዓት የበየነ መረብ ነጻነት እጅግ የሚበዛ ይመስላል፡፡