በዮርዳኖስ የፕሬስ እና ሕትመት ሕግ [1] በበይነመረብ (Internet) ላይ ሐሳብን የመግለጽ መብትን እንዲያደግድ ተደርጎ ትላንት [መስከረም 2/2005] እንዲሻሻል ተደረገ፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት ሕጉን ከሚያፀድቁበት ፓርላማ ፊት ለፊት ጋዜጠኞች እና የነፃ ሐሳብ አራማጆች ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡
እንደመሪ ቃል “የበይነመረብ ነፃነት” የሚል ባነር የያዙት በነፃ ሐሳብን የመግለጽ መብት አራማጆች በዮርዳኖስ የበይነመረብን ሞት አዝማሚያ ጠቁመዋል፡፡ የበይነመረብ ቀብር ለተባለለት ለዚህ አዋጅ ሰልፈኞቹ ጥቁር ልብስ ለብሰው ነበር፡፡
የፀደቀው ሕግ አሁንም በሥራ ላይ ለመዋል፣ የላዕላይ ፓርላማውን ፈቃድ እና ሕጎች ሁሉ በዮርዳኖስ በተግባር ላይ ከመዋላቸው በፊ የሚያስፈልጋቸው የዳግማዊ ንጉሥ አብዱላህን ፊርማን ይጠብቃል፡፡ ጀሚል ኒመሪ የተባሉ፣ አዋጁን የተቃወሙ የፓርላማ አባል፣ አዋጁን ከመቃወምም ባሻገር ሰልፉ ላይም ተሳትፈዋል፡፡ እንደርሳቸው አባባል እንዲህ ዓይነት አዋጆች ነፃነትን በመገደብ የሕዝቦችን ድምጽ ብቻ ለማፈን ይጠቅማሉ፡፡
አዲሱ ሕግ በይነመረብን ቅድመምርመራ እና ቁጥጥር የሚያጋልጥ ነው፤ የድረአምባዎች (websites) ባለቤቶችን በመንግስት እንዲመዘገቡ እና ‹‹ልክ እንደሌሎቹ ሕትመቶች›› ፈቃድ እንዲያወጡ ይጠይቃል፡፡ የድረአምባዎች ባለቤቶች አንባቢዎቸው ድረአምባዎቻቸው ላይ ለሚለጥፏቸው አስተያየቶች ሳይቀር ኃላፊነቱን ይወስዳሉ፡፡
በረቂቅ አዋጁ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ የተነሳበት ሲሆን፣ ወዲያውም በመረብዜጎች (netizens) ሚያስከትለው ጦስ ዙሪያ ትኩረትን ለመሳብ በሚል የመስመር ላይ እንቅስቃሴን [2] አስጀምሯል፡፡
በትዊተር ላይ፣ የመረብ ዜጎች ብስጭታቸውን በጽሑፍ ገልጸዋል፡፡
ሞሐመድ አልቃድ በትዊቱ [አረብኛ]
ይህንን ፎቶግራፍ ያጋራው ከሰልፉ ቦታ ሆኖ ነው፡፡
ኒዛር ሳማሪም በበኩሉ:
@godotbasha ደግሞ:
@godotbasha [6]: እና አሁን በዮርዳኖስ እና በአገሪቷ ፖሊስ መካከል ንፅፅር #ከሳንሱር ጉዳይጋ ባስቀምጥ በወንጀል እጠየቃለሁ ማለት ነው? #freenetjo
ሐሺም አል ባላውነህም በትዊቱ፡
ሐኒን አቡ ሻማትም፡
@HaninSh [8]: ከ#FreeNetJO ድራማ በስተጀርባ ምን አለ? ሴኔቱ (ላዕላይ ምክርቤቱ) እኮ መጀመሪያ ሊያፀደቀው ይገባል…. እኔ የማምነው ሴኔተሮቻችንን እንጂ ከንቱ የፓርላማ አባሎቻችንን አይደለም 🙂 #JO
የሻህዘይዶ ምላሽ፤
@Shahzeydo [9]: ኋላ በሚቆጩበት ሕግ የዮርዳኖሳውያን አስተዳደር የዮርዳኖስን የዕውቀት ምጣኔ ኃብት ላይ ማዕቀብ ጣለበት፡፡ ‘አጀብ’ የመንግስት አመክንዮ እየወደቀ ነው፡፡ #FreeNetJo”
ማጅ ዮሴፍም ቀጥሎ:
ፋዲ ዛገሞት አስተያየት ሲሰጥ:
ሞሐመድ ሻዋሽም ሲያስጠነቅቅ:
مش قادر اعبر اكتر عن امتعاضي – مجلس النواب الأردني انتو لعبتو بالنار
ባሽር ዚዳን አዲሱን የነፃነት ጥቃት ከዮርዳኖሳውያን የበይነመረብ ፀደይ ጋር ያያይዘዋል፡፡ እሱ እንደሚለው፡
@BasharZeedan [13]: መንግስት ከ#ዮርዳኖሳውያን_ ፀደይ ጀምሮ እስካሁን እየጨቆነ፣ ቅድመምርመራ እያደረገ እና እያፈነ ቆይቷል… ጉዳዩ አልገባቸውም
እናም ኦማር ቁዳህ ሲጨምርበት:
ኦማር ካመል ምርጫውን ለማስተጓጎል እንደተወሰደ የእርምጃ ደወል ይመለከተዋል፡
አቀንቃኞች በAvaaz.com [16] ላይ “በይነመረብን አድን” በሚል ዳግማዊ ንጉሥ አብዱላህ፣ የመረጃ ሚኒስትር እና የፓርላማ አባላት በፕሬስ እና ሕትመት ሕጉ ማሻሻይ ላይ ድጋሚ እንዲያስቡ የሚጠይቅ ፊርማ ማሰባሰብ ተጀምሯል፡፡
ሒዩማን ራይትስ ዋች በበኩሉ፣ በዮርዳኖሳውያን ድረአምባዎች ላይ ዕቀባ ለመጣል የፓርላማውን ይሁንታ ባገኘው አዋጅ ዙሪ ያ “ዮርዳኖስ፤ በመስመር ላይ ሐሳብን የመግለፅ መብትን ቀድሞ ወደመመርመር እየሄደች ነው ” የሚል ሪፖርት [17] አውጥቷል፡፡