ኢራን፤ “የእስልምና ወታደሮች” የካርቱኒስቱን የፌስቡክ ገጽ መዘበሩ

ዝነኛው ካርቲኒስት ማና ናዬስታኒ ማክሰኞ መስከረም 11 ፣ 2012 ራሳቸውን  “የእስልምና ወታደሮች” ብለው በሚጠሩ የስርዓቱ ደጋፊ ሰርጎ ገቦች ተመዘበረ፡፡ ሰርጎ ገቦቹ  በራሳቸው የፌስቡክ ገጽ  “ፈጣሪ ይመስገን ፤ የማና ናዬስታኒን የፌስቡክ ገጽ በቁጥጥር ስር አዋልነው” የሚል መልእክት በመለጠፍ(አሁን ተነስቷል) ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

ቡድኑ በናዬስታኒ ገጽ እስራኤል ካናዳ እና አሜሪካንን ጨምሮ ሌሎች ሀገሮችን የሚቃወሙ በርካታ ካርቱኖች እና ስዕሎች ለጥፏል፡፡ናዬስታኒ በጣም ተወዳጅ ካርቱኒስት ሲሆን የደጋፊዎቹ ገጽ 70,000 “መፍቀሬዎችን” አስተናግዷል፡፡የአለም ድምጾች የእርሱን በርካታ ካርቱኖች ሲያትም በ2006 ፀደይ በአወዛጋቢ ካርቱኑ ምክንያት የደረሰበትን  እስርንም ዘግቧል፡፡

ከሰርጎ ገቦቹ ካርቱኖች አንዱ ካናዳ ከኢራን ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማቋረጥ ከመወሰኗ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ርዕሱ “የካናዳ ኢምባሲ መዘጋት በኢራን ላይ ያለው ተጽእኖ” ሲሆን ካርቱኑ ደግሞ  ምንም የማይፈድ መሆኑን ያሳያል፡፡

በሌላ ካርቱን  ሚዲያው ለምን ለሶሪያን ዜና ሽፋን እየሰጠ የባህሬን የከለከለበትን ምክንያት ጠይቀዋል፡፡

የማና ናዬስታኒ ገጽ በስርዓቱ ደጋፊ የፕሮግራም ሰርጎ ገቦች ከተመረጠባቸው ምክንያቶች አንዱ ምንአልባት እንደ ማርዶማክ ባሉ የኢራናውያን መካናት ባሉት ፖለቲካዊ ካርቱኖቹ ሳይሆን አይቀርም፡፡ከቅርብ ጊዜ ካርቱኖቹ አንዱ በማርዶማክ የታተመው በቴህራን ስለተካሄደው   የገለልተኞች ጉባኤ ይናገራል፡፡

 

የተቀዋሚን መካነ ድር እና ጦማሮችን መመዝበር አዲስ ስልት አይደለም፡፡ የእስልምና ወታደሮች ከመከሰታቸው በፊት የኢራናውያን የመረጃ መረብ ጦር በበርካታ አገሮች የሚገኙ መካነ ድሮች ላይ ኢላማውን ማሳካቱ የሚያሳየው በየነ መረብ በትክክል ድንበር አልባ መሆኑና እንደትዊተር ያለ ትልቅ ስም ያላቸው መካነ ድሮች ሳይቀር ባልታወቁ በአጥቂዎች ሊንኮታኮቱ እንደሚችሉ ነው፡፡

በኢራን የፌስቡክ ገጾችን መመዝበር ፣ ካርቱኒስቶችን ማሰርና ሌሎች  አፈናዎች  ዐሳብን በነጻነት የመግለጽን  ፍላጎት በመግታት ረገድ ከሽፈዋል  ፤ በመስመር ላይም ሆነ ከመስመር ውጭ ፡፡

1 አስተያየት

ንግግሩን ይቀላቀሉ

አዘጋጅ፣ እባክዎ መግቢያ »

መመሪያዎች

  • ሁሉም አስተያየቶች በገምጋሚ ይታያሉ. አስተያየትዎን ከአንድ ጊዜ በላይ አይላኩ አለዚያ እንደ ስፓም ይታብዎታል.
  • እባክዎ ሌሎችን በአክብሮት ያናግሩ. ጥላቻ የሚያንጸባርቁ፣ ተሳዳቢ እና ግለሰብን የሚያጠቁ አስተያየቶች ተቀባይነት የላቸውም.