ታሪኮች ስለ ከሰሃራ በታች
ለዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ድጋፍ እና አጋርነት ለማሳየት ለሀምሌ 24 በተዘጋጀው ትዊተር ማራቶን ላይ በመካፈል አጋርነቶዎን በተግባር ያሳዩ::

በአወዛጋቢው የጸረ ሽብር አዋጁ እና ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ በመሞከር ወንጀሎች ስልጣን ላይ ባለው የኢትዮጵያ መንግስት ተጠርጥረው በእስር ላይ ለሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ድጋፍ እና አጋርነት ለማሳየት ሀምሌ 24 የትዊተር ላይ ማራቶን ተዘጋጅቷል:: ይህንንም ማራቶን በመቀላቀል ለጦማርያኑ እና ለ ጋዜጠኞቹ ያሎትን አጋርነት በተግባር ያሳዩ::
ኢትዮጵያውያኖች የብሔራዊ ቴሌቪዥናቸውን ‹ውሸቶች› በኤፕሪል ዘ ፉል ቀን አፌዙበት
ኢትዮጵያውያኖች የማሞኛ (አፕሪል ዘ ፉል) ቀንን በትዊተር ላይ በመንግሥት በሚተዳደረው የአገር ውስጥ ብቸኛ የቴሌቭዥን ጣቢያቸው (ኢቴቪ) ባስመሰሏቸው የውሸት አርዕስተ ዜኛዎች እንደንፁህ የወንዝ ወራጅ ውሃ በሚንኮለኮል ትዊቶች አጥለቅልቀውት እየተሳለቁ ቀኑን አክብረዋል፡፡
ኢትዮጵያዊቷ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ በእስር 1000 ቀን ሞላት
መጋቢት 7/2006 ኢትዮጵያዊቷ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ የታሰረችበት 1000ኛ ቀን ነው፡፡ ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ ተብላ የአምስት ዓመት ፅኑ እስራት ከተበየነባት ጥር 2004 ጀምሮ በእስር ላይ ትገኛለች፡፡
‘ጋናን ጡመራ’ የተሰኘ የማኅበራዊ አውታር የመጀመሪያ መሰባሰቢያ ቋት እየመተመሠረተ ነው
"በአካል የመገናኛ ስፍራው (ቋቱ) ልምድ ያላቸው የስብስቡ (ቡድኑ) አባላት ለተማሪዎች እና ለባለሙያዎች ሥልጠና መስጠት የሚያስችላቸውን ዕድል ለመስጠት ረዥም መንገድ ይጓዛል፡፡"
ኢትዮጵያውያን #SomeoneTellSaudiArabia በሚል ስደተኞች ላይ የደረሰውን እርምጃ ተቃወሙ
ጥቅምት 25፣ 2005 ሳኡዲ አረቢያ በሕገወጥ ስደተኞች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረች፡፡ ሳኡዲአረቢያ 7 ሚሊዮን የሚሆኑ የውጭ ዜጋ ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸውን አስጠልላለች ተብሎ ይታመናል፡፡
የ‘ወንድም ጋሼ’ አፍሪካዋ ቤቲ ላይ የባሕል እሴት ጥያቄ ተቀሰቀሰባት
የ‘ወንድም ጋሼ’ አፍሪካ (Big Brother Africa) የተሰኘው የእውነተኛ የኤቴሌቪዥን ትዕይንት የዘንድሮው (እ.ኤ.አ. 2013) ኢትዮጵያዊት ተሳታፊዋ መምህርት ቤቲ (Betty) ከሴራሊዮናዊው ተሳታፊ ቦልት (Bolt) ጋር ወሲብ ፈፅማለች የሚለው ዜና ከወጣ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በሁለት ወገን የጦፈ የባሕል እና የሞራል ጥያቄዎችን በማንሳት እየተሟጎቱ ነው፡፡
የበይነመረብ ዘመቻ በኢትዮጵያ ስለ ሰላማዊ ሰልፍ እና ዴሞክራሲ
ዞን ዘጠኝ ተብሎ በሚጠራው የጦማሪዎች እና አራማጆች ኢ-መደበኛ ቡድን አስጀማሪነት በርካታ የኢትዮጵያ ማኅበራዊ አውታር ተጠቃሚዎች ከሚያዝያ 30 እስከ ግንቦት 2/2005 ድረስ የዘለቀ የበይነመረብ ዘመቻ አድርገው ነበር (የዘመቻው ጋዜጣዊ መግለጫ እዚህ አለ)፡፡ ዘመቻው ለቡድኑ ሦስተኛው ሲሆን፣ ‹‹ዴሞክራሲን በተግባር እናውል፤ የሰላማዊ ሰልፍ መብት ይመለስ›› የሚል መሪ ቃል ላይ ተንተርሶ መንግሥት ‹‹በቀጥታና በተዘዋዋሪ›› እያደረገው ነው የተባለውን እገዳ ነገር ግን በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የተፈቀደውን ‹‹ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፣ የመሰብሰብና አቤቱታ የማቅረብ መብት›› ራሱ መንግሥት እንዲያከብረው የሚጠይቅ ዘመቻ ነበር፡፡ በዘመቻው የተለያዩ ጦማሮች የተጻፉ ሲሆን፣ በተወሰኑ ሰዓቶች ልዩነት አብዛኛው የዘመቻው ተሳታፊ የሚያጋራቸው አጫጭር ጽሑፎች ተለጥፈዋል፣ ተሳታፊዎች ለዘመቻው የተዘጋጀውን የፕሮፋይል ምስል እንዲቀይሩ ተጋብዘው እንደተጠየቁት አድርገዋል፣ የዘመቻውን ሒደት እንዲከታተሉ የዘመቻው የኹነት ገጽ ተፈጥሯል፣ ባለፉት ዓመታት ውስጥ የተከለከሉ ሰልፎች የጊዜ መሥመር ተዘጋጅቶ ታትሟል፤ በተጨማሪም በአንድ ደቂቃ ተኩል ቪዲዮ መብቱ ለዜጎች እንዲከበር ተጠይቋል፡፡ ከፌስቡክ በተጨማሪም በትዊተር ላይ #Demonstration4Every1 እና #Assembly4Every1 በሚሉ ኃይለ ቃሎች ተሳታፊዎች ሐሳባቸውን ገልጸዋል፡፡
ጅቡቲ፤ ‘ዲሞክራሲያዊ’ ምርጫን ተከትሎ የመጣው እስር
ትንሽ አገር ነገር ግን በአፍሪካ ቀንድ እጅግ በጣም ስትራቴጂክ አገር በሆነችው ጅቡቲ የየካቲት 15፣ 2005 አገር አቀፋዊ ምርጫን ተከትሎ በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ታሰሩ፡፡ በምርጫው ‹የሕዝቦች አንድነት ለዕድገት› (People's Rally for Progress) የተሰኛው ፓርቲ በድጋሚ ድልን ተቀዳጅቷል፡፡ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኡመር ጉሌህ ጅቡቲን እ.ኤ.አ ከ1999 ጀምሮ የመሩ ሲሆን በምርጫውም የ80 በመቶ መራጮች ድምፅ ቢያገኙም በከፍተኛ ሁኔታ በማጭበርበር ተጠርጥረዋል፡፡ እስሩ የመጣውም በዚሁ ማጭበርበር ጉዳይ [fr] ላይ ዜጎች ሰልፍ በመውጣታቸው ነው፡፡ እንደየጅቡቲ ሰብኣዊ መብት ሊግ እና የዓለምአቀፍ ሰብኣዊ መብት ፌደሬሽን ከሆነ 90 ሰዎች በአሰቃቂነቱ በሚታወቀው ጋቦዴ ማዕከላዊ እስር ቤት ታጉረዋል፡፡ እስሩ ይህ ጽሑፍ እስከተጻፈበት ሚያዚያ 20005 ድረስ ቀጥሏል፡፡
በኬኒያ ቴሌቭዥን የተላለፈ የኮንዶም ማስታወቂያ የሃይማኖት ተቋማትን አስቆጣ
በቅርቡ ለህዝብ አገልግሎት ይውል ዘንድ HIV እና ተዛማጅ በሽታዎችን ለመከላከል የተላለፈ የኮንዶም ማስታወቂያ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትን ማስቆጣቱን ተከትሎ በመገናኛ ብዙሃን እንዳይተላለፍ ታገዷል፡፡ ማስታቂያው አንዲት ባለትዳር ሴት ባለቤቷ ከትዳር ውጪ በሚያደርጋቸው የግብረስጋ ግንኙነቶች ኮንዶም እንዲጠቀም ምክር ስትሰጠው የሚያሳይ ሲሆን ማስታወቂያው የኬኒያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዩኤስ ኤድ እና ዩኬ ኤድ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎለት የተዘጋጀ ነው፡፡
ስለፍቅርና የፍቅር ጨዋታ ከአንጎላ
ወጣቷ ሮዚ አልቬስ አንጎላዊ ጦማሪ (cronista) ናት፡፡ መኖሪያዋን ያደረገችው በአንጎላ ዋና ከተማ ሉዋንዳ ውስጥ ነው፡፡ “cronista” ማለት በፖርቱጋል ቋንቋ መጦመር የሚለውን ቃል ተስተካካይ ትርጉም የሚሰጥ ሲሆን - ፅሁፎቹ ባብዛኛ ጊዜ በጋዜጣ የሚታተሙ ታሪኮች አንዳንዴ እውነተኛ ተሪኮች ሌላ ጊዜ ደግሞ የፈጠራ ልብ ወለዶች ሲሆኑ ብዙውን ጊዜ የራስ ችሎታን በአጭሩ ያሳያሉ፡፡ “Sweet Cliché" በተሰኘው ጦማሯ አልቬስ አጫጫር ታሪኮችን የምትፅፍ ሲሆን፣ በአብዛኛው ስለፍቅር እና ስለፍቅር ጥብቅ ግንኙነቶች ትፅፋለች ( Bolgspot የፅሑፎቿ እንባቢዎች እድሜቸው ለፅሑፉ የሚመጥን ስለመሆኑ ያስጠነቅቃል)፡፡ከዚህ በታች ሰሞኑን በጣም አነጋጋሪ የነበረው ፅሑፏ ቀርቧል፡፡