ታሪኮች ስለ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መካነ ድር ተመዘበረ

  1 ጥቅምት 2012

በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ የሚገኘው የሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መካነ ድር እራሳቸውን  ራሳቸውን አርቲን ሐከርስ ብለው በሚጠሩ ሰርጎ ገቦች ተመዘበረ፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ  መካነ ድሮች ሲመዘበሩ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በ2012 እ.ኤ.አ ብቻ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፐሬሽን፣ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታስቲክስ  ባለስልጣን እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ሌሎች መካነ ድሮች ተመዝብረዋል፡፡   ይህን ተከትሎ...

ኢትዮጵያ፤ በእስር ላይ ያለውን ጦማሪ እስክንድር ነጋን ማስታወስ

ሐምሌ 6/2004 የኢትዮጵያ ፌዴራል ፍርድ ቤት ጦማሪው እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችንም 23 የተቃውሞ ተግባር የፈፀሙ ሰዎችን ለ18 ዓመታት እና ሌላ መጠን ያለው የእስር ፍርድ ከአሸባሪነትጋ በተያያዘ በይኖባቸዋል፡፡ እስክንድር ነጋ የተቃውሞ ሐሳቦቹን መተንፈሻ ለማግኘት የመስመር ላይ ጦማሪ የሆነ ጋዜጠኛ ሲሆን መጨረሻ ጊዜ ከታሰረ አንድ ዓመት ሞላው፡፡ መስከረም 4/2005 የታሰረበት አንደኛ ዓመት ነበር፡፡ የኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ማኅበረሰብ በፌስቡክ ላይ አስታውሶታል፡-

ታንዛኒያ፣ ኢትዮጵያ፤ መለስ ዜናዊ ከመቃብር ውስጥ ትዊት እያደረጉ ነው

  9 መስከረም 2012

"ከዚያ በኋላ ድንገት@PMMelesZenawi (መለስ ዜናዊ) ጣልቃ ገቡ፤ ከሞት በኋላ ለታንዛኒያው የፓርላማ አባል ዢቶ ካብዌ መልስ መስጠት ጀመሩ:: @PMMelesZenawi: @zittokabwe እባክዎ ከኔ የተሻለ ይሁኑ፡፡ እዚህ ቀልድ የለም፤ ዋጋዬን ልከፍል እየተዘጋጀሁ ነው" የሚለው መልስ በታንዛኒያ ከፍተኛ ውይይት ፈጠረ::