ታሪኮች ስለ ኢትዮጵያ
ለተቃዋሚዎች፣ የዓለም ጤና ድርጅት እጩ ሊቀ መንበሩ የኢትዮጵያን ጨቋኝ መንግሥት ነው የሚወክሉት
በአገራቸው መንግሥት እንደተገለሉ የሚሰማቸው ኢትዮጵያውያን ዶ/ር ቴድሮስ እንዳይመረጡ የኢንተርኔት ዘመቻ እያደረጉ ነው።
የኦሮሚያው ተቃውሞ #OromoProtests በተቀሰቀሰ ማግስት ኢትዮጵያ የበይነመረብ ግንኙነትን ቆለፈች

#OromoProtests content on social media has triggered many attempts by the government to limit digital traffic and block telecom services in Oromia.
የኦሮሞ ሙዚቀኞችን የማፈን አሳፋሪ ገመና
የመንግሥት ሳንሱርን ለመስበር አማራጭ ይዞ የመጣውን ኢንተርኔት በመጠቀም፣ በዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ ዩቱዩብ እና ፌስቡክ ላይ በተደረገ ቆጠራ ብቻ ከ300 በላይ ፖለቲካ ነክ ዘፈኖች ከ2006 ወዲህ የተለቀቁ መሆኑ የፖለቲካ ዘፈኖች መነሳሳት አለ ብሎ ለማለት ያስችላል፡፡
ኢትዮጵያ ‹ታይቶ ከማይታወቀው› የኢኮኖሚ ዕድገቷ በተፃራሪ ረኀብ ተጋርጦባታል
"ከኢትዮጵያ ውስጥ በተገኘ መረጃ መሠረት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች “ረኀብ፣ ችጋር ወይም ሞት” የሚሉ ቃላቶችን በምግብ ጥያቄዎቻቸው ውስጥ እንዳያካትቱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡"
ተማሪዎች የዋና ከተማዋን የመስፋፋት ዕቅድ ለምን ይቃወማሉ?
"በዐሥር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ገበሬዎችን የሚያፈናቅል፣ ኑሯቸውን የሚያጠፋ እና ማንነታቸውን የሚያንኳስሰውን ይህንን ዕቅድ ይዞ መቀጠል በጣም የሚያሳዝን ነው የሚሆነው፡፡ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ተማሪዎች ለገበሬዎቹ ጥቅም ሲሉ ነው ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ያስቀመጡት"
የኢትዮጵያ ዞን ፱ ጦማሪያን የአለምአቀፍ ህግ ድክመቶች ተጋርጦባቸዋል

የዞን ፱ ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ባለስልጣን የአለምአቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ደረጃዎችን -- እና እንዲያውም ብሔራዊ ህጉንም ጨምሮ -- የሚተገብሯቸው ወይም ችላ የሚሏቸው እንዳሻቸው መሆኑን ያረጋገጠ ነው።
ለዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ድጋፍ እና አጋርነት ለማሳየት ለሀምሌ 24 በተዘጋጀው ትዊተር ማራቶን ላይ በመካፈል አጋርነቶዎን በተግባር ያሳዩ::

በአወዛጋቢው የጸረ ሽብር አዋጁ እና ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ በመሞከር ወንጀሎች ስልጣን ላይ ባለው የኢትዮጵያ መንግስት ተጠርጥረው በእስር ላይ ለሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ድጋፍ እና አጋርነት ለማሳየት ሀምሌ 24 የትዊተር ላይ ማራቶን ተዘጋጅቷል:: ይህንንም ማራቶን በመቀላቀል ለጦማርያኑ እና ለ ጋዜጠኞቹ ያሎትን አጋርነት በተግባር ያሳዩ::
ኢትዮጵያውያኖች የብሔራዊ ቴሌቪዥናቸውን ‹ውሸቶች› በኤፕሪል ዘ ፉል ቀን አፌዙበት
ኢትዮጵያውያኖች የማሞኛ (አፕሪል ዘ ፉል) ቀንን በትዊተር ላይ በመንግሥት በሚተዳደረው የአገር ውስጥ ብቸኛ የቴሌቭዥን ጣቢያቸው (ኢቴቪ) ባስመሰሏቸው የውሸት አርዕስተ ዜኛዎች እንደንፁህ የወንዝ ወራጅ ውሃ በሚንኮለኮል ትዊቶች አጥለቅልቀውት እየተሳለቁ ቀኑን አክብረዋል፡፡
ኢትዮጵያዊቷ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ በእስር 1000 ቀን ሞላት
መጋቢት 7/2006 ኢትዮጵያዊቷ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ የታሰረችበት 1000ኛ ቀን ነው፡፡ ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ ተብላ የአምስት ዓመት ፅኑ እስራት ከተበየነባት ጥር 2004 ጀምሮ በእስር ላይ ትገኛለች፡፡
ኢትዮጵያውያን #SomeoneTellSaudiArabia በሚል ስደተኞች ላይ የደረሰውን እርምጃ ተቃወሙ
ጥቅምት 25፣ 2005 ሳኡዲ አረቢያ በሕገወጥ ስደተኞች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረች፡፡ ሳኡዲአረቢያ 7 ሚሊዮን የሚሆኑ የውጭ ዜጋ ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸውን አስጠልላለች ተብሎ ይታመናል፡፡