ታሪኮች ስለ Asia

ቋንቋዎች ነጻ ናቸው? የዓለም አቀፉን የአፍመፍቻ ቋንቋ የሚመለከቱ ሐሳቦች

  19 የካቲት 2014

ዛሬ የዓለምአቀፍ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀን ነው፡፡ ቀኑ በUNESCO አባል አገራት የቋንቋ እና ባሕል ልዩነቶችን እና ብዝኃቋንቋዊነትን ለማበረታታት ይከበራል፡፡ ዕለቱ በተለይም በባንግላዴሽ እ.ኤ.አ. ከ1952 ጀምሮ ‹ኤኩሼ የካቲት› በመባል የሚታወቀው የቋንቋዎች ንቅናቄ ቀንን ዕውቅና ለመስጠት ነው፡፡ ዕለቱ የካቲት 14 (ፌብሩዋሪ 21) ተደርጎ የተመረጠው በባንግላዴሽ (የዛኔዋ ምስራቅ ፓኪስታን) በዕለቱ እ.ኤ.አ. በ1952 በዳካ...

ሕንድ፤ ባሎች ሚስቶቻቸውን ለማጀት ሥራቸው ሊከፍሏቸው ነው?

  15 መስከረም 2012

የህንድ የሴቶችና ሕፃናት ሕብረት ዕድገት ሚኒስቴር ያወጣው ረቂቅ አዋጅ በፓርላማው ከፀደቀ፣ ሚስቶች በቤት ውስጥ ለሚሰሩት ሥራ ባሎች ውጪ ሰርተው ከሚያገኙት ውስጥ የተወሰነ መጠን ለሚስቶቻቸው እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ይሆናል፡፡ በሚኒስቴሩ ዕቅድ መሰረት፣ ሚስቶች በቤት ውስጥ የሚሰሩት ስራ ዋጋ የሚለካበት ሞዴል የተዘጋጀ ሲሆን፣ በዚሁ መሰረት የቤት ውስጥ ሥራ የሚሰሩትን ሰዎችና ሥራቸው ለኢኮኖሚው ያለውን ተዋፅዖ ዕውቅና መስጠት ይቻላል፡፡

ቻይና በአፍሪካ፤ እውነተኛው ታሪክ

  10 መስከረም 2012

የቻይና ትኩረት በአፍሪካ ላይ በከፍተኛ ፍጥነት የጨመረው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሲሆን አሁን አገሪቱን የአፍሪካ ትልቋ የንግድ ሸሪክ አድርጓታል፡፡ “በቻይና እና አፍሪካ መካከል የተደረገው የንግድ ልውውጥ ባለፉት 5 የ2012 ወሮች ውስጥ የዓመት ለዓመት ንፅፅሩ በ22 በመቶ ሲያድግ መጠኑ 80.5 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ” በማለት የቻይና የንግድ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ማይክ ኪንግ ጽፏል፡፡