ታሪኮች ስለ ላቲን አሜሪካ
በመካነ አእምሮ ቅርጽ ሀገር በቀል ዕውቀትን ፍለጋ በቦሊቪያ
“ምስጋና ለቅደመ አያቶቻቸን ተጋድሎ ይህ ዩኒቨርሲቲ [...] ህያው ሆኗል፡፡”
የአንድ ቬንዙዌላዊ አገርበቀል ዩንቨርስቲ ውስጣዊ ምልከታ
የቬንዙዌላ አገርበቀል ዩንቨርስቲ ተማሪ መሆን ምን ይመስላል? ከትምህርታዊ ተግባቦት የወጡ ሦስት ተማሪዎች በእያደጉ ያሉ ድምፆች ትዕይንተ ሥራ ላይ ዲጂታል ፎቶዎችን እንዴት ማንሳት፣ በይነመረብ ላይ መስቀል እና ማጋራት እንደሚቻል ለመማር ተሳትፈው ነበር፡፡ እነዚህ ሦስት ተማሪዎች፣ በዚህ ልዩ ዩንቨርስቲ ውስጥ ከቬንዙዌላ ማኅበረሰብ የተውጣጡ እና በይነባሕላዊ እና ተግባራዊ የትምህርት ዓይነቶችን እንዲለዋወጡ የሚደረገው ጥረት ማሳያ ናቸው፡፡ በመንግሥታዊው ኢንፎሴንትሮስ [es] የተሰኘ ፕሮግራም በተዘጋጀው የዩንቨርሲቲውን የሳተላይት ግንኙነት በመጠቀም ተማሪዎቹ እንቅስቃሴዎቻቸውን፣ ንብረቶቻቸውን እና አስደናቂ ውበት የተላበሰውን እና በቦሊቪያ ውስጥ 2,000 ሄክታር ላይ የተንጣለለውን ካምፓሳቸውን በበይነመበረብ አጋርተዋል፡፡