ታሪኮች ስለ ሴቶችና ስርዓተ ጾታ ከ መስከረም, 2012

ኡጋንዳ፤ ከአሥራዎቹ ዕድሜ ያልተሻገረች ሴት የአፍሪካ ትንሽዋ የፓርላማ አባል ሆነች

  27 መስከረም 2012

አፍሪካ እና የአፍሪካ ሴቶች የምር እያደጉ ነው:: የማላዊ እና የላይቤሪያ ፕሬዚደንቶች ሴቶች ናቸው:: አሁን ደግሞ ኡጋንዳ በዕድሜ ትንሽዋን የ19 ዓመትዋን ሴት የፓርላማ አባል ፕሮስኮቭያ አሌንጎት ኦሮሚያት መርጣለች::

ሕንድ፤ ባሎች ሚስቶቻቸውን ለማጀት ሥራቸው ሊከፍሏቸው ነው?

  15 መስከረም 2012

የህንድ የሴቶችና ሕፃናት ሕብረት ዕድገት ሚኒስቴር ያወጣው ረቂቅ አዋጅ በፓርላማው ከፀደቀ፣ ሚስቶች በቤት ውስጥ ለሚሰሩት ሥራ ባሎች ውጪ ሰርተው ከሚያገኙት ውስጥ የተወሰነ መጠን ለሚስቶቻቸው እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ይሆናል፡፡ በሚኒስቴሩ ዕቅድ መሰረት፣ ሚስቶች በቤት ውስጥ የሚሰሩት ስራ ዋጋ የሚለካበት ሞዴል የተዘጋጀ ሲሆን፣ በዚሁ መሰረት የቤት ውስጥ ሥራ የሚሰሩትን ሰዎችና ሥራቸው ለኢኮኖሚው ያለውን ተዋፅዖ ዕውቅና መስጠት ይቻላል፡፡