ታሪኮች ስለ ስፖርት ከ ጥቅምት, 2012
ኢትዮጵያ አሸነፈች፤ ልጆቿም የእርግብ አሞራ እያሉ ፈነጠዙ
የወያኔ ካድሬዎችን ያህል በሕዝብ ደስታ የሚበሳጭ አንድ ፈልጎ ማግኘት ይቸግራል። ምነው ሸዋ፣ ዛሬኳ ቢተውን ምነው?! አሁን ማን ይሙት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ለኳሱ ምን አበርክተው ነው ይሄ ሁሉ የታሪክ ሽሚያ? ማስታወሻነቱማ የሚገባው ብርድና ሃሩር ሳይል ለኣመታት መከራውን የበላው ሕዝብ ነው።
ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያውያን የቡድናቸውን ማሸነፍ በጉጉት እየተጠባበቁ ነው
ምንም እንኳን የእግርኳስ ውጤት በአብዛኛው በጨዋታዎች እለት በሚፈጠሩ ክስተቶች ላይ ጥገኛ ቢሆንም ታሪክ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ያደላል። የሱዳን ብሄራዊ ቡድን ከሜዳው ውጪ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ባደረጋቸው ያለፉት ዘጠኝ ጨዋታዎች በአንዱም ያላሸነፈ ሲሆን በአጠቃላይ ሁለቱ ቡድኖች ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ባደረጓቸው ሶስት የማጣሪያ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ሶስቱንም ጨዋታዎች አሸንፋ ሰባት ጎሎችን ተጋጣሚዋ ሱዳን ላይ ስታስቆጥር፤ የተቆጠረባት አንድ ጎል ብቻ ነው።