ታሪኮች ስለ የንግግር ነፃነት

ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያውያን የቡድናቸውን ማሸነፍ በጉጉት እየተጠባበቁ ነው

ምንም እንኳን የእግርኳስ ውጤት በአብዛኛው በጨዋታዎች እለት በሚፈጠሩ ክስተቶች ላይ ጥገኛ ቢሆንም ታሪክ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ያደላል። የሱዳን ብሄራዊ ቡድን ከሜዳው ውጪ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ባደረጋቸው ያለፉት ዘጠኝ ጨዋታዎች በአንዱም ያላሸነፈ ሲሆን በአጠቃላይ ሁለቱ ቡድኖች ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ባደረጓቸው ሶስት የማጣሪያ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ሶስቱንም ጨዋታዎች አሸንፋ ሰባት ጎሎችን ተጋጣሚዋ ሱዳን ላይ ስታስቆጥር፤ የተቆጠረባት አንድ ጎል ብቻ ነው።

14 ጥቅምት 2012

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መካነ ድር ተመዘበረ

በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ የሚገኘው የሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መካነ ድር እራሳቸውን  ራሳቸውን አርቲን ሐከርስ ብለው በሚጠሩ ሰርጎ ገቦች ተመዘበረ፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ  መካነ ድሮች ሲመዘበሩ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በ2012 እ.ኤ.አ...

1 ጥቅምት 2012

ኢራን ጎግል እና ጂሜል እንዳይታዩ አገደች

እገዳው የተላለፈበተት ምክንያት ህዝቡ ብዙዎች እንደ ስድብ ቃል የሚያዩት በዩቱዩብ የሚገኘውን ጸረ እስላም ፊልም እንዲቃወሙ ነው (ዩቲዩብ የጎግል ንብረት ነው)፡፡ ኮራማባዲ “የወንጀል ይዘት ያላቸው ቅጽበቶች ድንጋጌ ኮሚሽን” ቁልፍ አባል ናቸው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ እንዳንዶች የጎግል መታገድ እውነተኛው ምክንያት ከመስከረም 22 ጀምሮ ስራ ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀውን እስካሁን ግን ብቅ ያላለውን የኢራናውያን ብሔራዊ በየነ መረብ የበለጠ ለማስተዋወቅ ነው ሲሉ ከወዲሁ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

27 መስከረም 2012

ኢራን፤ “የእስልምና ወታደሮች” የካርቱኒስቱን የፌስቡክ ገጽ መዘበሩ

ዝነኛው ካርቲኒስት ማና ናዬስታኒ ማክሰኞ መስከረም 11 ፣ 2012 ራሳቸውን “የእስልምና ወታደሮች” ብለው በሚጠሩ የስርዓቱ ደጋፊ ሰርጎ ገቦች ተመዘበረ፡፡ ሰርጎ ገቦቹ በራሳቸው የፌስቡክ ገጽ “ፈጣሪ ይመስገን ፤ የማና ናዬስታኒን የፌስቡክ ገጽ በቁጥጥር ስር አዋልነው” የሚል መልእክት በመለጠፍ(አሁን ተነስቷል) ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

14 መስከረም 2012