ታሪኮች ስለ ዲጂታል አራማጅነት

ኢራን፤ “የእስልምና ወታደሮች” የካርቱኒስቱን የፌስቡክ ገጽ መዘበሩ

ዝነኛው ካርቲኒስት ማና ናዬስታኒ ማክሰኞ መስከረም 11 ፣ 2012 ራሳቸውን “የእስልምና ወታደሮች” ብለው በሚጠሩ የስርዓቱ ደጋፊ ሰርጎ ገቦች ተመዘበረ፡፡ ሰርጎ ገቦቹ በራሳቸው የፌስቡክ ገጽ “ፈጣሪ ይመስገን ፤ የማና ናዬስታኒን የፌስቡክ ገጽ በቁጥጥር ስር አዋልነው” የሚል መልእክት በመለጠፍ(አሁን ተነስቷል) ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

ዮርዳኖስ: ፓርላማው በይነመረብን የሚገድብ አዋጅ የሚያጸድቅበት ቀን ሐዘን

አዲሱ ሕግ በይነመረብን ቅድመምርመራ እና ቁጥጥር የሚያጋልጥ ነው፤ የድረአምባዎች (websites) ባለቤቶችን በመንግስት እንዲመዘገቡ እና ‹‹ልክ እንደሌሎቹ ሕትመቶች›› ፈቃድ እንዲያወጡ ይጠይቃል፡፡ የድረአምባዎች ባለቤቶች አንባቢዎቸው ድረአምባዎቻቸው ላይ ለሚለጥፏቸው አስተያየቶች ሳይቀር ኃላፊነቱን ይወስዳሉ፡፡