ታሪኮች ስለ Culture

የእምቢተኝነት ዘፈኖች በኢትዮጵያ ቢታፈኑም እየበረቱ ነው

የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ የአደባባይ ተቃውሞዎቹን ቢያስቆምም፣ የእምቢተኝነቱ ስሜት እና ትርክት ግን ሳይነካ አሁንም አለ። የኦሮምኛ ዘፋኞች ጉልህ - እና ተደማጭ - የተቃውሞ ንቅናቄው ማነቃቂያ ሆነው እያንሰራሩ ነው።

20 ሐምሌ 2017

የኦሮሞ ሙዚቀኞችን የማፈን አሳፋሪ ገመና

የመንግሥት ሳንሱርን ለመስበር አማራጭ ይዞ የመጣውን ኢንተርኔት በመጠቀም፣ በዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ ዩቱዩብ እና ፌስቡክ ላይ በተደረገ ቆጠራ ብቻ ከ300 በላይ ፖለቲካ ነክ ዘፈኖች ከ2006 ወዲህ የተለቀቁ መሆኑ የፖለቲካ ዘፈኖች መነሳሳት አለ ብሎ ለማለት ያስችላል፡፡

8 ጥር 2016

ኢትዮጵያውያኖች የብሔራዊ ቴሌቪዥናቸውን ‹ውሸቶች› በኤፕሪል ዘ ፉል ቀን አፌዙበት

ኢትዮጵያውያኖች የማሞኛ (አፕሪል ዘ ፉል) ቀንን በትዊተር ላይ በመንግሥት በሚተዳደረው የአገር ውስጥ ብቸኛ የቴሌቭዥን ጣቢያቸው (ኢቴቪ) ባስመሰሏቸው የውሸት አርዕስተ ዜኛዎች እንደንፁህ የወንዝ ወራጅ ውሃ በሚንኮለኮል ትዊቶች አጥለቅልቀውት እየተሳለቁ ቀኑን አክብረዋል፡፡

8 ሚያዝያ 2014

የNSA ስለላን በተመለከተ ካርቱኖች ይላኩና፣ 1000 ዶላር ይሸለሙ

ዘ ዌብ ዊ ወንት ካርቱኒስቶችን፣ የዲዛይን ፈጣሪዎችን እና አርቲስቶችን መልሰን የምንታገልበት ቀን በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 11፣ 2014 የበይነመረብ ስለላን እና የግለሰብ ደኅንነት መብትን በተመለከተ ወጥ የካርቱኖች ውድድር ውስጥ እንዲሳተፉ...

3 የካቲት 2014

ቪዲዮ፤ “ኖ ዉማን፣ ኖ ድራይቭ” ሳኡዲ አረቢያን አደመቃት

ዛሬ፣ ጥቅምት 16፣ 2006 ለሳኡዲ አራማጆች በኪንግደሙ ሴቶች መኪና እንዳይነዱ የተጣለባቸው ማዕቀብ ላይ ለማመጽ የመረጡት ቀን ነበር። የማኅበራዊ አውታር ተጠቃሚዎች በአገሪቷ ውስጥ መኪና እየነዱ ስለታዩት ሴቶች ቁጥር መጨመር በስፋት እያወሩ...

31 ጥቅምት 2013

የ‘ወንድም ጋሼ’ አፍሪካዋ ቤቲ ላይ የባሕል እሴት ጥያቄ ተቀሰቀሰባት

የ‘ወንድም ጋሼ’ አፍሪካ (Big Brother Africa) የተሰኘው የእውነተኛ የኤቴሌቪዥን ትዕይንት የዘንድሮው (እ.ኤ.አ. 2013) ኢትዮጵያዊት ተሳታፊዋ መምህርት ቤቲ (Betty) ከሴራሊዮናዊው ተሳታፊ ቦልት (Bolt) ጋር ወሲብ ፈፅማለች የሚለው ዜና ከወጣ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በሁለት ወገን የጦፈ የባሕል እና የሞራል ጥያቄዎችን በማንሳት እየተሟጎቱ ነው፡፡

9 ሰኔ 2013

የአንድ ቬንዙዌላዊ አገርበቀል ዩንቨርስቲ ውስጣዊ ምልከታ

የሚያድጉ ድምጾች

የቬንዙዌላ አገርበቀል ዩንቨርስቲ ተማሪ መሆን ምን ይመስላል? ከትምህርታዊ ተግባቦት የወጡ ሦስት ተማሪዎች በእያደጉ ያሉ ድምፆች ትዕይንተ ሥራ ላይ ዲጂታል ፎቶዎችን እንዴት ማንሳት፣ በይነመረብ ላይ መስቀል እና ማጋራት እንደሚቻል ለመማር ተሳትፈው ነበር፡፡ እነዚህ ሦስት ተማሪዎች፣ በዚህ ልዩ ዩንቨርስቲ ውስጥ ከቬንዙዌላ ማኅበረሰብ የተውጣጡ እና በይነባሕላዊ እና ተግባራዊ የትምህርት ዓይነቶችን እንዲለዋወጡ የሚደረገው ጥረት ማሳያ ናቸው፡፡ በመንግሥታዊው ኢንፎሴንትሮስ [es] የተሰኘ ፕሮግራም በተዘጋጀው የዩንቨርሲቲውን የሳተላይት ግንኙነት በመጠቀም ተማሪዎቹ እንቅስቃሴዎቻቸውን፣ ንብረቶቻቸውን እና አስደናቂ ውበት የተላበሰውን እና በቦሊቪያ ውስጥ 2,000 ሄክታር ላይ የተንጣለለውን ካምፓሳቸውን በበይነመበረብ አጋርተዋል፡፡

20 መጋቢት 2013